መልዕክተ ቹቸ
00:00
00:00
Embed Code (recommended way)
Embed Code (Iframe alternative)
Please login or signup to use this feature.

መልዕክተ ቹቸቤ ክፍል ሁለት ቁጥር አሥራ አራት ብዙ ቁም ነገሮችን አካቶ ቀርቦአል። አዝናኝነቱ እንደተጠበቀ ነው፣ አስተማሪነቱም እንደዚያው ብዙ ጥልቅ ቁምነገሮችን የያዘ ነው። የትግራይ አፍራሽ ኃይል በዘርና በሀይማኖት ለመከፋፈልና ለማጫረስ እናም ገላጋይ ለመሆን ያደረገው ሙከራ ይበልጥ የሚያፋቅር፣ የሚያስተሳስብና ይህ ከፋፋይ ኃይል መንገድ የሳተ አምባገነን ሳይሆን ከመነሻው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነቱን አምርሮ የሚጠላ ጠላት መሆኑን ሕዝብ በሚገባ እየተረዳው እንዲመጣ አመቻችቷል። ቢሆንም አደገኛውንና ቤተሰብን፣ የስራ ባልደረባን፣ ዘመድ ወዳጅን ሁሉ በጥርጣሬ መነጽር ውስጥ በመክተት ፈሪ፣ ሽባና ተስፋ የቆረጠ ሕዝብ እንዲኖር እየተደረገ ነው። አንድ ለአምስት በበርካታ መጥፎ ተብለው በተፈረጁ ስርዐቶች ውስጥ አምባ ገነኖች የተጠቀሙበት ማፈኛ መንገድ ነው። በዚህ ስለላ ምክንያት ብዙ ሰዎች እንደወጡ ቀርተዋል። የሚያሳዝነው አስገዳዮቹ የቅርብ ጓደኞች የቤተሰብ አባላት ጉዳቱን ባለማወቅ በሰጡት መረጃ ምክንያት ነው። ብዙዎች ሰካራምና ወፈፌ እንዲሆኑ የተገደዱትም ተናግረው የማይናገሩት አዝነው ያማያባሩት ፀፀት በውስጣቸው ስለሚኖር ነው። አምባ ገነኖችም ይህንኑ እንደ ማስፈራርያ መልሰው እየተጠቀሙበት ገዝተው ለመኖር ይመቻቸዋል። አንድ ለአምስት ሳይሆን አንድ ለአራት ቢባል ጥሩ ይፈታዋል። ምክንያቱም አንድ ሰው አራት ሰዎችን የሚሰልልበት ሳይሆን አራት ሰዎች በአንድና በተመሳሳይ ጊዜ አንድን ሰው የሚሰልሉበት የአፈና መሳርያ መሆኑን እንመለከታለን። ፍቅራችንን እንዳንነጠቅ ሳቃችንን እንዳንቀማ ደግሞ በጣም እንስቃለን። መልካም ጊዜ።

Licence : All Rights Reserved


X